thumbnail

Topic

Technologies and technical equipment for agriculture and food industry

Volume

Volume 69 / No. 1 / 2023

Pages : 335-348

Metrics

Volume viewed 0 times

Volume downloaded 0 times

RICE MECHANIZATION IN ETHIOPIA: TRENDS, AND PROSPECTS

በኢትዮጵያ የሩዝ ሜካናይዜሽን: አዝማሚያዎች እና ተስፋዎች

DOI : https://doi.org/10.35633/inmateh-69-31

Authors

(*) Tikuneh DESSYE

Ethiopian Institute of Agricultural Research

Woldesenbet LAIKE

Ethiopian Institute of Agricultural Research

(*) Corresponding authors:

[email protected] |

Tikuneh DESSYE

Abstract

The domestic rice industry of Ethiopia is constrained by low productivity, poor quality, and old processing machines. The rice production system is done by hand or with rudimentary tools, and only 2% of households have access to tractors. It takes 175 labor days to weed and 66% of the total farm operations. Rice harvesting and threshing are done manually using a serrated sickle and animal trembling respectively. Farmers are responsible for most of the pre-milling operations and store paddy for household consumption in local stores. Challenges include fragmented farm holdings, poor marketing channels, and a lack of awareness of post-harvest utilization. The prospects for rice mechanization development include improving the rice mechanization research system, training local entrepreneurs, providing repair and maintenance services, promoting custom hiring centers, local manufacturing of farm implements, organizing agricultural cooperatives, landholding, and land ownership structures, assessing foreign experience, linking importers and service providers, and encouraging investments in the rural infrastructure.

Abstract in Amharic

የኢትዮጵያ የሩዝ ምርት በዝቅተኛ ደረጃ፣ በጥራት ጉድለት እና በአሮጌ ማቀነባበሪያ ማሽኖች የተገደበ ነው። የሩዝ አመራረት ሂደት በእጅ ወይም በቀላል የግብርና መሳሪያዎች የሚከናዎን ሲሆን 2 በመቶው የሚሆኑት አምራቾች ብቻ ትራክተር ተጠቃሚ ናቸው። አረም ማረም በእጅ በመንቀል የሚተገበር፣ ብዙ ጉልበት የሚጠይቅና አንድ ሰው አንድ ሄክታር ለማረም 175 የስራ ቀናት የሚጨርስበት ሲሆን ይህም ከጠቅላላው የእርሻ ስራ 66 በመቶውን ይይዛል። የሩዝ ሰብል የማጨድ ስራ የሚከናወነው በእጅ በተሰራ ማጭድ በመጠቀም ነው፣ አብዛኞቹ የሩዝ ቅድመ ማቀነባበር ስራዎች ደግሞ በአርሶ አደሮች ብቻ የሚከወኑ ናቸው። አብዛኛዎቹ ገበሬዎች ጀንፈል ሩዝን ለቤተሰብ ፍጆታ የሚያከማቹት ደግሞ በአካባቢው በተለመዱ የባህላዊ የምርት ማስቀመጫ ዕቃዎችን በመጠቀም በቤታቸው ውስጥ ነው። ከዋና ዋና የሩዝ ሜካናይዜሽን ተግዳሮቶች መካከል የተበታተኑ የእርሻ ማሳ ይዞታዎች፣ ደካማ የግብይት አሰራሮች እና የድህረ ምርት አጠቃቀም ግንዛቤ ማነስ ጥቂቶቹ ናቸው። የሩዝ ሜካናይዜሽን እድገትን ለማሻሻል ከሚያግዙ ዕድሎች ውስጥ ደግም የሩዝ ሜካናይዜሽን የምርምር ሥርዓትን ማሻሻል፣ የአገር ውስጥ ቴክኖሎጅ አምራቾችን ማብቃት፣ የግብርና ማሽነሪዎች ጥገናና የመገጣጠም አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ማጠናከር፣ የግብርና ማሸነሪ አገልግሎት ሰጪ ማዕከላትን ማስፋፋት፣ የእርሻ መሣሪያዎችን በአገር ውስጥ ማምረት፣ የግብርና ኅብረት ሥራ ማኅበራትን ማደራጀት፣ የመሬት ይዞታና የመሬት ባለቤትነት መዋቅሮችን ማሻሻል፣ የተሻሻሉ የሌሎችን ሀገራትን ልምድ በመገምገምና መቅሰም፣ አስመጪ እና አገልግሎት ሰጪዎችን ማጠናከር እና በገጠር መሠረተ ልማት ውስጥ ኢንቨስትመንቶችን ማበረታታት ይገኙበታል።

IMPACTFACTOR0CITESCORE0

Indexed in

Clarivate Analytics.
 Emerging Sources Citation Index
Scopus/Elsevier
Google Scholar
Crossref
Road